Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 2 ሺህ 424 የላብራቶሪ ምርመራ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2424 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ አንድ (11) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ የሁሉም እድሜያቸው ከ19 እስከ 47 ዓመት የሆኑ ወንዶች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ አስታውቅዋል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 8 ሰዎች ከአፋር ክልል (ሰመራ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል (መቐለ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) እና 1 ሰው አማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ለይቶ ማቆያ) የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው መሆናቸውንም ዶክተር ሊያ በሪፖርታቸው አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት 1 ሰው ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገመ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 106 ደርሷል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ39 ሺህ 48 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 261 ደርሷል።

አሁን ላይ 148 ሰዎች በህክምና ላይ ሲሆኑ፥ እስካሁንም 106 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፤ የ5 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው ጃፓን መመለሳቸው ይታወሳል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.