Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሣለፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቶ ውሣኔ አሣልፏል።

ካቢኔው የክልሉ የህብረተሰብ ልማት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤትን እንደገና ለማደራጀት የቀረበውን ደንብ ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል።

ፕሮጀክቱ የክልሉን የተፈጥሮ ጸጋዎች ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በመቀየር የህብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዓላማ ተደርጎ የተቋቋመ ነው ተብሏል፡፡

የክልሉ ካቢኔ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ በተጠናከረ መልኩ ተደራጅቶ ዓላማውን እንዲያስፈጽም የሚያስችል ደንብ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

ፕሮጀክቱ በአሶሳ ከተማ ዋና ማስተባባሪያ እንደሚኖረውና እንደአስፈላጊነቱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችም የሚኖሩት ይሆናል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ፕሮጀክት ጽ/ቤቱን እና በስሩ የሚቋቋመውን የኢንቨስትመንትና የንግድ ድርጅቶችን እንቅስቃሴን በበላይነት የሚመራ ቦርድ ተቋቁሟልም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ካቢኔው በክልሉ በእርሻ ሥራ ላይ የተሠማሩ ባለሃብቶችን ለማበረታታት የሚውል መመሪያ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.