Fana: At a Speed of Life!

ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር እየተደረገ ያለው ዝግጅት የሚበረታታ ነው -አቶ ጣሂር መሃመድ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር እየተደረገ ያለው ዝግጅት የሚበረታታ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ ገለጹ፡፡

በጎንደር ጥምቀትን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፥ በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማ ለሚመጡ እንግዶች የአውሮፕላን በረራ በብዛት ለማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ጥምቀት በጎንደር አይከበርም በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው ያሉት አቶ ጣሂር÷ ሃይማኖታዊ መሰረቱን በጠበቀ መንገድ እንዲከበር ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በፋሲለደስ ጥምቀተ ባሕር የተሟላ የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የክልሉን የሀገር ውስጥ የጎብኚ ፍሰት ለመጨመር የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ በበኩላቸው÷ ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር የተለያዩ ተቋማትን ያሳተፈ ኮሚቴ ተቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጀመሩን አንስተዋል።

በዓሉን መሰረት አድርጎ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ከባለሃብቶች ጋር መግባባት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል።

ጎንደር እንግዷቿን ለመቀበል እየተሰናዳች መሆኑን ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል።

በጎንደር ፋሲለደስ ጥምቀተ ባሕር ቅጥር ግቢ የፅዳት ዘመቻ በከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ሃይማኖት አባቶችና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች መካሄዱም ተጠቁሟል፡፡

በምናለ አየነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.