ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት የመግባቢያ ሥምምነት ሠነድ መፈራረሟ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት መሆኑ ተነገረ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት የመግባቢያ ሥምምነት ሠነድ መፈራረሟ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ነው ሲል ሰርቫይቭ ዘ ኒውስ ገለጸ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የትብብርና የአጋርነት መግባቢያ ሠነድ መፈራረማቸው ይታወቃል፡፡
ይህም የመግባቢያ ሠነድ የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት ዕውን የሚያደርግ፣ የባሕር በር አማራጮቿን የሚያሠፋ እንዲሁም የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናክር ነው ተብሏል፡፡
ዘገባው ከዚህ ጋር አያይዞ እንዳለው፤ ፖሊሲን በማደስ ከወደብ አልባነት ጋር ተያይዞ ያለው የዕድገት ማነቆ እና በፍጥነት እየጨመረ የመጣው የሕዝብ ቁጥር የሚያስከትለውን የፖለቲካ ቀውስ በኢትዮጵያ ግንዛቤ ማግኘቱን ጠቅሷል።
ይህንን አስቀድሞ ለመከላከል በማሰብም የባህር በር ባለቤትነት ላይ ሲሰራ መቆየቱን አመልክቷል።
እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ያላት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በጅቡቲ ብቻ የተገደበ እንደሆነ የሚያነሳው ዘገባው፥ ለዚህም ከባድ የወደብ ክፍያ እንደምትፈጽም ገልጿል።
ይህም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ባለው እድገት የበለጠ ሸክም እንደሆነባት ነው የተጠቀሰው፡፡
የአሁኑ ሥምምነትም እነዚህን ሸክሞች የሚያቀልና ሀገሪቱ የጀመረችውን እድገት እንድትቀጥል አስተዋጽዖ እንዳለው ተመላክቷል በዘገባው፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!