Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሳዳት ጀማል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሳዳት ጀማል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ሳዳት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በተለያዩ ክለቦች በግብ ጠባቂነት ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ በመሆን አገልግሏል፡፡

የቀድሞ ተጫዋችና አሰልጣኝ ሳዳት ጀማል በገጠመው ህመም የህክምና ርዳታ ሲደረግለት ቆይቶ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሳዳት ጀማል ህልፈት የተሰማውን እጅግ ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድና ለእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.