Fana: At a Speed of Life!

በውጭ ሀገራት የ’’ወደ ሀገር ቤት ጉዞ ጥሪ’’ እንቅስቃሴ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ የሚኖሩ ሁለተኛው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲጓዙ በተለያዩ ሀገራት ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በውጭ ለሚኖሩ ሁለተኛ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ጥሪውን ተከትሎም ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው እንዲጓዙ በተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን የወከሉ ሚሲዮናውያን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ጋር በመሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

የኖርዲክ ሀገራት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ፥ ጥሪው ኢትዮጵያውያኑ በብዙ የሚያተርፉበት በመሆኑ ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እየተሰተራ ነው።

አክለውም ፥ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሀገር ቤት ጉዞ ጥሪ ወደ ሀገራቸው የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አባቶቻቸው የገነቧትን ሀገር በጥልቀት እንዲያውቁና ጥብቅ ትስስር እንዲፈጥሩ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ወደ መጡባቸው ሀገራት ሲመለሱም ያዩትን ለሌሎች በማጋራት የሀገራቸው አምባሳደር ጭምር በመሆን የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል፣ ሃብት የሚያስተዋውቁበት እንዲሁም በጎ ገፅታዋንም የሚገነቡበት እንደሆነም ነው ያነሱት።

የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፥ ባሉባቸው ሀገራት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ እንደመሆናቸው በሀገራቸው የልማት እንቅስቃሴ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ዕድል ይፈጥርላቸዋል ብለዋል አምባሰደሩ፡፡

በተጨማሪም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳብ አመንጭነት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ተካተው የለሙ የቱሪስት መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በማድረግ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ መነቃቃትን ይፈጥራልም ነው ያሉት።

በቀጣይም የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ተጨማሪ መረጃዎችን የማሰራጨት፣ በሦስቱም ፕሮግራሞች ተጓዦችን የመመዝገብ እንዲሁም የክትትል ተግባራት እንደሚከናወኑ አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡

በምራኦል ከድር

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.