Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው ዶክተር መቅደስ ዳባ ሹመት አጽድቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዶክተር መቅደስ ዳባ የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን አፅድቋል፡፡

ዶክተር መቅደስ ዳባ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው የተጣለባቸው ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃለ-መሃላ ፈጽመዋል።

ዶክተር መቅደስ ዳባ በማኅጸንና ጽንስ ሕክምና ባደረጉት ምርምርና አስተዋጽዖ በፈረንጆቹ 2021 በሴቶች ዘርፍ የዓለም የጽንስና ማኅፀን ሕክምና ሽልማትን ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.