Fana: At a Speed of Life!

ሸበሌ ዞን የግብርና ዘርፍ ስብራታችንን ለመጠገን የጀመርነው ጉዞ ውጤታማ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሸበሌ ዞን የግብርና ዘርፍ ስብራታችንን ለመጠገን የጀመርነው ጉዞ ውጤታማ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ቤርዓኖ ወረዳ በአርሶ አደሮች፣ ባለሀብቶች እና በመንግሥት እየተሠሩ ያሉ የመስኖ ግብርና ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ዋቢ ሸበሌ ወንዝን በመጠቀም በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ቤርዓኖ ወረዳ እየተሠራ ያለውን የመስኖ ግብርና ሥራ ዛሬ ተመልክተናል ብለዋል፡፡

በአካበቢው እየተሰራ ያለው የመስኖ ግብርና ስራ የግብርና ዘርፍ ስብራትታችንን ለመጠገን የጀመርነው ጉዞ ውጤታማ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በአካባቢው የዋቢ ሸበሌ ወንዝን በመጠቀም ለገበያ የሚሆን እና ለምርጥ ዘር ብዜት የሚያገለግል ሰፋፊ የግብርና ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.