Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጃፓን በትምህርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ጃፓን የትምህርት ዘርፉን ለማጠናከር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሽባታ ሂሮኖሪ ጋር ተወያይተው በየትምህርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) አራት የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ገንብቶ እንደሚያስረክብም ስምምነት መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል።

አምባሳደር ሽባታ ሂሮኖሪ ሀገራቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለማገዝና ከጃፓን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለማስተሳሰር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በምርምር ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራትና ፕሮፌሰሮች የሚያደርጉትን የልምድ ልውውጥ ለመደገፍ ፍላጎት አለን ነው ያሉት፡፡

ጃፓን 20 በሂሳብና በሳይንስ ትምህርቶች ላይ የሚሰሩ በጎ ፈቃደኞች ወደ ኢትዮጵያ እንደምትልክም ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.