Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን ማጠቃለያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰኔ 26 ቀን 2016 ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር የቆየው 26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን ማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ዳያስፖራዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

26ኛው ዓለም አቀፍ የሐረር ቀን በልማት ፕሮጀክቶች ምረቃ፣ በሲምፖዚዬም፣ በባህል ኤግዚቢሽን፣ በስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሁም አብሮነትና አንድነትን በሚያጠናክሩ ሁነቶች ሲከበር መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በበጎ ፍቃድ አገልግሎት፣ በጉብኝቶች እና ሌሎች ሁነቶች በድምቀት መከበሩን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.