ፕሬዚዳንት ሣሕለወርቅ ከአየርላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይና መከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ ከአየርላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይና የመከላከያ ሚኒስትር ሚሼል ማርቲን ጋር ተወያዩ።
በሚሼል ማርቲን የተመራ ልዑክ በትናንትናው ዕለት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለትም ፕሬዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራውን ልዑክ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በተመሳሳይ ዛሬ ረፋድ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከልዑኩ ጋር በርከት ባሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።