በደሴ በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የተገነባው ዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ምርቱን ማከፋፈል ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታህሣሥ 17 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደሴ ከተማ በቀዳሚዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተገነባው የዳቦና ዱቄት ፍብሪካ ለሥራ እድል ፈጠራ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተመላክቷል፡፡
ፋብሪካው ዳቦ የማከፋፈል ሥራውን በዛሬው ዕለት የጀመረ ሲሆን÷በከተማዋ በሚገኙ አምስቱም ክፍለ ከተሞች ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን መኮንን እንደተናገሩት÷ ፋብሪካው ምርቶቹን ወደ ማህበረሰቡ ከማቅረብ ባሻገር ለበርካታ ወጣቶች የሥራ እድል ፈጥሯል።
የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው ፋብሪካው የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አንጻር ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተው÷ከዳቦ አቅርቦት በተጨማሪ ለማህበረሰቡ ዱቄት እያቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።
ፋብሪካው ምርቱን ለተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ከማቅረብ ባሻገር ለብዙዎች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉንም ጠቅሰዋል።
ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ 30 የማከፋፈያ ማዕከላት የሚኖሩት ሲሆን÷በቀን 300 ሺህ ዳቦና 420 ኩንታል ዱቄት ማምረት እንደሚችል ተገልጿል።
በከድር መሃመድ