Fana: At a Speed of Life!

በይዞታቸው ላይ የማልማት ጥያቄ ያቀረቡ 31 አርሶ አደሮች ተፈቀደላቸው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በይዞታቸው ላይ የማልማት ጥያቄ ላቀረቡ 31 አርሶ አደሮች እንዲያለሙ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አሥተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከከተማው ዕድገት አብረው ማደግ ሲገባቸው ከልማቱ ሲገፉ የነበሩ በከተማው ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮችን ጥያቄ ለመመለስ እየተሠራ መሆኑንም ቢሮው ገልጿል፡፡

በለውጡ መንግሥት አርሶ አደሮች በያዙት ይዞታ ላይ እራሳቸውን ችለው እንዲያለሙ ወይም በጋራ ማልማት እንዲችሉ በሕግ መብት መሰጠቱን ያስታወሰው ቢሮው፤ በዚሁ መሠረት የቢሮው እስትራቴጂክ ካውንስል በይዞታቸው ላይ የማልማት ጥያቄ ላቀረቡ 31 አርሶ አደሮች ምላሽ ሰጥቷል።

በመሆኑም አርሶ አደሮቹ በ16 ነጥብ 75 ሔክታር ላይ በግብርና፣ ንግድ እና በተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንዲሠማሩ ወስኗል ተብሏል፡፡

ውሳኔው አርሶ አደሩ ከከተማው ልማት ጋር አብሮ ሕይወቱን እንዲቀይር ከማስቻሉ ባሻገር ሌሎች አርሶ አደሮችን የሚያበረታታ እና የከተማ አሥተዳደሩን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.