Fana: At a Speed of Life!

በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የትጥቅ ትግልን የሚቃወም ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፋግታ ለኮማ ወረዳ የትጥቅ ትግልን የሚቃወምና ሰላማዊ አማራጮችን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍና የሰላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች መሳተፋቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በመርሐ ግብሩ የተገኙት አቶ ግዛቸው ሙሉነህ÷ የትጥቅ ትግልን መርጠው ጫካ የገቡ ሃይሎች ሕዝቡ ላይ እያደረሱት ያለው ጫና ከፍተኛ መሆኑንና የልማትና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች እንዲደናቀፉ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ሕዝቡ እነዚህን ሃይሎች ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመሆን መታገል በመጀመሩ በርካታ አካባቢዎች ወደ ሰላም መመለሳቸውን ገልጸው÷ መንግሥት የክልሉን ሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።

የወረዳው ምክትል አሥተዳዳሪ ታገል እጅጉ በበኩላቸው÷ ሕዝባዊ ሰልፍና የሰላም ኮንፈረንሱ ሕዝቡ ሰላም ፈላጊ መሆኑን የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎችም አሁን ያለው ሰላም ዘላቂ እንዲሆን ከመንግሥት ጎን ለመቆም ቁርጠኛ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.