በመዲናዋ የጥምቀት በዓል በሚከበርባቸው አካባቢዎች የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሚከበርባቸው አካባቢዎች የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበው የጥምቀት በዓል በድምቀት እንዲከበር ለማስቻል ‘የጥምቀትን በዓል በንጹህ ጎዳና’ በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ አድርገዋል።
በዚህም የከተራ እና የጥቅምት በዓል የሚከበርበትን ጃን ሜዳን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ማህበር ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል።
በዘመቻው የሁሉም ክፍለ ከተሞች ወጣቶች ማህበራት፣ በጎ ፈቃደኞች እና ሌሎች የህበረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በዓሉን ታሳቢ በማድረግ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ሰራተኞች፣ የኃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የጽዳት ዘመቻ ተከናውኗል።