Fana: At a Speed of Life!

አቶ አረጋ ከበደ የደሴ ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎበኙ

‎አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በደሴ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

የአመራር አባላቱ የጎበኙት በከተማዋ ከቧንቧ ውሃ-ሮቢት- ወሎ ባህል አምባ እየተገነባ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ነው፡፡

የኮሪደር ልማቱ የብስክሌትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ ሌሎች መዝናኛ ሥፍራዎችን በማካተት እየተገነባ ሲሆን አሁን ላይ የአስፋልት ማንጠፍ ስራው ተጀምሯል።

ይህ የኮሪደር ልማት 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዳለው ተመላክቷል፡፡

በኮሪደር ልማት ሥራው የከተማዋ ማህበረሰብ በገንዘብ፣ በጉልበትና በዕውቀቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ መገለጹን የዘገበው ኢዜአ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.