ከሚጠበቅብን በላይ ለመሥራት እንተጋለን- አቶ ኦርዲን በድሪ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተሰጡ ግብረ መልሶች መሰረት ከሚጠበቅብን በላይ ለመሥራት እንተጋለን ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
ርዕሰ መሥተዳድሩ በሐረሪ ክልል እያስመዘገብነው ላለው የልማት ሥራ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍና ክትትል ዐቅም ሆኖኗል ብለዋል።
በቀጣይም የተሰጡንን ግብረ መልሶች ተግባራዊ በማድረግ ከሚጠበቅብን በላይ ለመሥራት ሌት ቀን የምንተጋ ይሆናል ሲሉ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል።
ለልማት ሥራዎች ስኬት ከፍተኛ እገዛ ላደረገው ለክልሉ ሕዝብም አመስግነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን መጎብኘታቸው ይታወቃል።