በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓትን ለማጠናከር እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓትን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፡፡
የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ደግነህ ቦጋለ እንዳሉት ÷ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ለፍትሕ ሥርዓት መረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡
በክልሉ የባሕል ሽማግሌዎች ፎረም መቋቋሙን ጠቁመው ÷ በዚህም በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ሰላም፣ አንድነት እና ዘላቅ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር እንዲፈጠር የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በክልሉ ሀገር በቀል እውቀቶች እና እሴቶችን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በትብብር እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የባሕል ሽማግሌዎች ፎረም በተለያዩ ሁኔታ የሚፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡
በተካልኝ ሃይሉ