Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ አስጀምሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የጽ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምጸሀይ ጳውሎስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በማስጀመሪያው የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ እና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።

በተጨማሪም በአበሽጌ ወረዳ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ፣ የአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እና የጽዱ ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነው የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ተጀምሯል፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ በዞኑ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.