Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ዞን ከ208 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባ የውሃ ፕሮጀክት ለአገልግሎት በቃ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ሻንቶ ከተማ ከ208 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በፕሮጀክቱ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሻንቶ ከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከ30 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል ነው የተባለው።

በከተማዋ ከዚህ ቀደም ከውሃ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ይነሳ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በመመለስ ረገድ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

በዕለቱ ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በከተማዋ ችግኝ ተተክሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.