Fana: At a Speed of Life!

አረንጓዴ ዐሻራ የአረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ያጠናክራል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር ሚናው የጎላ ነው አለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡

ሚኒስቴሩ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስጀምሯል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ በተጀመረው የክረምት በጎ ፍቃድ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትን ጨምሮ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ይደረጋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሀኑ ፀጋዬ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሀገሪቷን የአረንጓዴ ልማት ዲፕሎማሲና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችል ነው፡፡

በጎረቤት ሀገራትና በአባይ ተፋሰስ ሀገራት የችግኝ ተከላን በማካሄድ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ በምሳሌነት የሚጠቀስ ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የአረንጓዴ ልማት ፕሮግራም የአፍሪካውያንን እህት ወንድሞች እውቅና በማግኘቱ ኢትዮጵያ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉባኤዎችን እንድታስተናግድ እድል ፈጥሯል ነው ያሉት፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በበኩላቸው፥ በከተማ አስተዳደሩ በተሰሩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ከ10 ሚሊዮን በላይ ችግኝ መተከሉን ጠቅሰዋል፡፡

ከ3ሺህ 600 በላይ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና አዳዲስ ቤቶች መሰራታቸውን እንዲሁም ከ86ሺ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የተለያዩ የትምህርት መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

በቲያ ኑሬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.