Fana: At a Speed of Life!

የከተሞችን ልማታዊ ሴፍቲኔት ለማጠናከር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞችን ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ።

የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ እና የ2018 ዕቅድ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ፈንታ ደጀን በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ለሴፍቲኔት ፕሮግራም ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን 45 ቢሊየን ብር ተመድቧል።

ይህም ተጨማሪ 699 ሺህ 112 ዜጎች የሴፍቲኔት መርሐ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን ነው ያስረዱት፡፡

በሴፍቲኔት ፕሮጀክት የበርካታ ዜጎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ከተረጂነት ወደ አምራችነት ማሸጋገር የሚያስችል ውጤት መመዝገቡን አመላክተዋል ።

የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ተጠቃሚዎች ተገቢውን የቢዝነስ ክህሎትና የቴክኒክ ስልጠና ወስደው በመረጡት የሥራ መስክ እንዲሰማሩና ውጤታማ እንዲሆኑ ይሰራል ብለዋል፡፡

በቤዛዊት ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.