Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞ የፋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ገሰሰ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀድሞ የሬድዮ ፋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ገሰሰ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል።

በ66 ዓመታቸው ከትናንት በስቲያ ያረፉት አቶ ሙሉጌታ÷ ሥርዓተ ቀብራቸው በመቐለ ፅርሃ አርያም ካቴድራል ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ነው የተፈጸመው።

አቶ ሙሉጌታ ከሬድዮ ፋና መስራች አመራሮች ውስጥ አንዱ የነበሩ ሲሆን፥ ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ሬድዮና በሜጋ አሳታሚ ድርጅት በኃላፊነት አገልግለዋል፡፡

የአንድ ሴት እና የሁለት ወንድ ልጆች አባት የነበሩት አቶ ሙሉጌታ፥ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በእንግሊዝ ሀገር ተከታትለዋል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በአቶ ሙሉጌታ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ፥ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.