ቼልሲ አሌሃንድሮ ጋርናቾን አስፈረመ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቼልሲ አርጀንቲናዊውን የክንፍ መስመር አጥቂ አሌሃንድሮ ጋርናቾን ከማንቼስተር ዩናይትድ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ጋርናቾ በሰባት ዓመት ውል በ40 ሚሊየን ፓውንድ ሒሳብ ነው ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ፊርማውን ያኖረው፡፡
አርጀንቲናዊው ወጣት ተጫዋች በማንቼስተር ዩናይትድ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የነበረ ቢሆንም አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድኑን ከተረከቡ ወዲህ የእቅዳቸው አካል አለመሆኑን ተከትሎ ከክለቡ ጋር መለያየቱ ተመላክቷል፡፡
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!