ዛሬ በኅብር ቀን ለ500 ሺህ የከተማችን ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ ጳጉሜን-2 በኅብር ቀን ለ500 ሺህ የከተማችን ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተናል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ የተከናወነው በመዲናዋ በማዕከላት ፣ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ነው።
በክረምቱ ወራት ምንም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካምችን፣ የሀገር ባለውለታዎችንና በዝቀተኛ ገቢ የሚተዳደሩ156 ሺህ ያህል የህብረተስብ ክፍሎችን ስንደግፍ ቆይተናል ብለዋል።
ወገኖቻችን በጊዜያዊ ችግሮች እንዳይጎዱ በተለያዩ መልኩ በመደገፍ በዘላቂነት ከድህነት ለመውጣት ሳምንቱን ሙሉ ዘላቂ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በመደጋገፍ ለማህበራዊ ችግር ተጋላጮች የምናደርገውን ድጋፍ ማጠናከር ይገባናል ያሉት ከንቲባዋ፥ ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶችና ለከተማዋ ወጣቶች ምስጋና አቅርበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!