ኢትዮጵያ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር የብር ሜዳልያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር የብር ሜዳልያ አገኘች።
ብርቱ ፉክክር በታየበት በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሁለተኛ በመውጣት ነው ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የብር ሜዳልያን ያስገኘው።
በውድድሩ ላይ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን በ6ኛነት ሲያጠናቅቅ አትሌት በሪሁን አረጋዊ 12ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
ውድድሩን ፈረንሳዊው ጂሚ ግረሴር በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ስዊድናዊው አንድሪያስ አልማግሪን በ3ኛነት ማጠናቀቅ ችሏል።
ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር እስካሁን ሦስት ሜዳሊያዎችን ማግኘት የቻለች ሲሆን÷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በማራቶን ውድድር የብር ሜዳልያ እንዲሁም አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 10 ሺህ ሜትር ነሐስ ሜዳልያ አግኝተዋል።