በክለቡ ታሪክ ከፍተኛ ገቢ ያገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ…
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት 666 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ በክለቡ ታሪክ ከፍተኛ ገቢ ማግኘቱን ነው ቢቢሲ የዘገበው፡፡
ለአምስት ዓመታት ከማልያ ላይ ስፖንሰር ከሆነው ስናፕድራገን ጋር ያደረገው ስምምነት ክለቡ ከፍተኛ ገቢ እንዲያገኝ እንዳስቻለው ተጠቁሟል፡፡
የክለቡ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦማር ቤራዳ ክለቡ ፈታኝ ጊዜ ላይ ሆኖ ሪከርድ የሆነ ገቢ ማግኘቱ የማንቼስተር ዩናይትድ መለያ የሆነውን ፅናት ያሳያል ብለዋል፡፡
በ2025/26 የውድድር ዓመት ክለቡን በሁሉም ዘርፍ ለማሻሻል ጠንክረው እየሰሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
ከሊጉ ደካማ የውድድር ዓመት በተጨማሪ በዩሮፓ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በቶተንሃም ተሸንፎ ዋንጫውን ማጣቱ አይዘነጋም፡፡
ከፈረንጆቹ 1973/74 በኋላ በክለቡ ታሪክ መጥፎ የሚባለውን ጊዜ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ያሳለፈው ማንቼስተር ዩናይትድ ዘንድሮም ጅማሮው ላይ ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ አይገኝም፡፡
በወንድማገኝ ፀጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!