Fana: At a Speed of Life!

ከ34 ዓመታት በኋላ ያለ ወርቅ የተመለሰው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ…

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃፓን ቶኪዮ ሲካሄድ የቆየው 20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ሁለት የብር እና ሁለት ነሐስ በድምሩ አራት ሜዳልያዎችን በማግኘት ውድድሩን አጠናቅቃለች።

ኢትዮጵያ ባገኘቸው የሜዳልያ ብዛት መሰረት አጠቃላይ ከተሳታፊ ሀገራት 21ኛ ደረጃ በመያዝ የቶኪዮ ቆይታዋን ቋጭታለች፡፡

በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪክ ከ34 ዓመታት በኋላ ያለ ወርቅ ሜዳልያ የተመለሰችበት ሻምፒዮና ሆኗል፡፡

አትሌት ትዕግስት አሰፋ በሴቶች ማራቶን እና አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች የብር ሜዳሊያ ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች እና ሲምቦ አለማየሁ በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የነሃስ ሜዳሊያ ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡

አሜሪካ 13 ወርቅ 5 ብር እና 4 ነሃስ በድምሩ 22 ሜዳሊያዎች በማግኘት ከዓለም 1ኛ በመሆን ሻምፒዮናውን በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

ኬንያ 7 ወርቅ 2 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 11 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ከዓለም 2ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ በቀዳሚነት ውድድሩን ጨርሳለች፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.