በአማራ ክልል ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ500 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ም/ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ተገኝተዋል።
በመድረኩ በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከ500 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ 452 ተማሪዎች ሽልማትና እውቅና እንደሚሰጣቸው ተመላክቷል።
ከእነዚህ መካከልም ሦስት ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች 400 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸው ነው የተገለጸው፡፡
የሽልማትና እውቅና ሥነ ሥርዓቱ ተሸላሚ ተማሪዎችን በማበረታታትና በመደገፍ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ተግተው በመስራት የሀገር አለኝታነታቸውን እንዲያሳዩ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡