Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በጎዳና ላይ ውድድሮች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የጎዳና ላይ ውድድሮች ድል ተቀዳጅተዋል።

በሮማንያ በተደረገ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን፥ በወንዶች አትሌት ከሀሪ ቤጂጋ እንዲሁም በሴቶች አትሌት መዲና ኢሳ በቀዳሚነት አጠናቅቀዋል።

በስፔን አልባሴቴ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፈዋል።

በወንዶች አትሌት ሀጎስ እዮብ በቀዳሚነት ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን፥ በሴቶች አትሌት ኪሮስ ሙአዝ አሸናፊ ሆናለች።

በጣሊያን የትሬንቶ ግማሽ ማራቶን አትሌት ሀብታምነሽ ተስፋይ በቀዳሚነት አጠናቅቃለች።

በካርዲፍ ግማሽ ማራቶን አትሌት ይስማው ድሉ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ሲያሸንፍ፥ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ፍቃዱ ሊቻ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቋል።

በሴቶች አትሌት አለም ንጉስ 2ኛ እንዲሁም አትሌት ውድነሽ አለሙ 3ኛ ወጥተዋል፡፡

በኮሎኝ ማራቶን የተሳተፈችው አትሌት ፋንቱ ሹጊ በቀዳሚነት አጠናቃለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.