Fana: At a Speed of Life!

ተቋማዊ ሪፎርሙ የፀረ ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ የመከላከል አቅምን አሳድጓል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የተከናወነው የፖሊስ ተቋም ሪፎርም በክልሉ የፀረ ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ የመከላከል አቅምን አሳድጓል አሉ የክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)።

ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዡ እንዳሉት፤ የክልሉ ፖሊስ የሕግ ማስከበር አቅሙን ለማጠናከር እና ለህዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል ሁለንተናዊ ሪፎርም አድጓል።

ሪፎርሙ ተቋማዊ አቅምን በማጠናከር የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት በማሻሻል ውጤታማ የሕግ ማስከበር ስራ ለማከናወን ያስችላል ነው ያሉት።

የፖሊስ ሥራዎችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና ግልጽ ለማድረግ የዲጂታል ለውጥ ሥራዎች ማድረጉንም ጠቁመዋል።

የፖሊስ መዋቅር የሰው ኃይል ምደባን በመመሪያና ስታንዳርድ መሠረት መፈጸሙን ጠቅሰው፤ ገለልተኛ የፖሊስ አገልግሎት፣ የሕዝብን አመኔታ እና ፍትሕን የማስፈን አቅምን ማጠናከር ላይ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።

ተቋማዊ ሪፎርሙ በክልሉ የተደራጁ ወንጀሎችንና የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ ለመከላከል የሚያስችል አቅምን እያሳደገ እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህም በክልሉ ሰላም እየሰፈነ በመምጣቱ የልማት ተግባራትን ጨምሮ የመማር ማስተማር ስራዎችን በተረጋጋ ሁኔታ ለማከናወን መቻሉን ተናግረዋል።

ለአርሶ አደሩ የግብርና ግብዓቶች በአግባቡ ተደራሽ በመሆናቸው የእርሻ ሥራው በጥሩ ሁኔታ መከናወን መቻሉን ገልፀዋል።

አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት ስልታዊ አቅጣጫ ማስቀመጡን ገልጸው፤ በዚህም የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

በክልሉ የውጭ ጠላት ተልዕኮን አንግበው የሚንቀሳቀሱ ባንዳዎችን የማፅዳት ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.