የፍርድ ቤት አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ እየተሰራ ነው – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፍርድ ቤት አገልግሎቶችን ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው አሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመደበኛ ችሎት አገልግሎት የመክፈቻ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እንዳሉት፤ የህግ ተርጓሚ አካላት ሥራዎችን በገለልተኝነትና በነጻነት እንዲያከናውኑ እየተሰራ ነው።
የህግ አሰራር ማሻሻያዎች፣ ምቹ የሥራ ከባቢ ለመፍጠር የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የዳኝነት ነጻነትን ከተጠያቂነት ጋር ዕውን በማድረግ ተዓማኒ ተቋማትን መገንባት ከሁሉም እንደሚጠበቅ ገልጸው፤ ፍትህን ማስፈን ትጋትን የሚጠይቅ ትልቅ ሀላፊነት እንደሆነ አንስተዋል።
በፌደራል ደረጃ የተጀመሩ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ሥራዎችም በሁሉም ደረጃ እንዲስፋፋ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው፤ የዳኝነት ነጻነት እና ገለልተኝነትን ለማጠናከር፣ አገልግሎቱን ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተገኝተዋል ነው ያሉት።
በበጀት ዓመቱ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ የማዘመን፣ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ የማድረግና በሂደት ላይ ያሉ የህግ ማዕቀፎችን የማሻሻል ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
እንዲሁም ምቹ የሥራ ከባቢን የመፍጠር ሥራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የዳኝነት አገልግሎት ስታንዳርድ ወደ ስራ ይገባል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!