ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ዛሬ ከሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር ተወያይተናል ብለዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ነው የገለጹት፡፡