የሠንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ኤምባሲዎች ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ኤምባሲዎች ተከብሯል፡፡
በቻይና፣ በፓኪስታን፣ በኩዌት፣ በሮም፣ በዚምባቡዌ፣ በፓሪስ፣ በጅቡቲ፣ በእስራኤል፣ በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ፅህፈት ቤቶች ቀኑን አክብረዋል።
‘ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፤ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ሁነቶች የተከበረ ሲሆን፤ ለሠንደቅ ዓላማ የሚሰጠው ክብርና ፍቅር ታስቧል።
እንዲሁም ሀገራዊ አንድነትና ህብረ ብሔራዊነት ለማፅናት እየተከፈለ ያለውን መስዋዕትነት በማሰብ ቀኑ ተከብሯል።