አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ የግማሽ ማራቶን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸንፏል።
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን ለመጨረስ 1 ሰዓት 01 ሰኮንድ ከ21 ማይክሮ ሰኮንድ ፈጅቶበታል፡፡
በሴቶች ዘርፍ በተደረገ ውድድር ደግሞ አትሌት መስከረም ማሞ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በሌላ ዜና በአምስተርዳም ማራቶን አትሌት ጸጋዬ ጌታቸው 2ኛ እንዲሁም አትሌት ጌታነህ ሞላ 3ኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል፡፡
አትሌት ጸጋዬ ጌታቸው ባለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ እንደነበር ይታወሳል፡፡