Fana: At a Speed of Life!

በተኪ ምርት ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ሶስት ወራት በተኪ ምርት 1 ነጥብ 08 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እንዳሉት ÷ በሩብ ዓመቱ የአምራች ዘርፉን ውጤታማነት ይበልጥ ለማሳደግ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም እና የሥራ እድል ፈጠራ ከማሳደግ አንጻር ተጨባጭ ውጤተ ተገኝቷል ብለዋል፡፡

በዚህም በሩብ ዓመቱ 37 አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መሸጋገራቸውን ነው ሚኒስትሯ ያስረዱት፡፡

የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሥራ ውጤታማነት እየተጠናከረ መሆኑን ጠቁመው ÷ ባለፉት ሶስት ወራት 10 ፋብሪካዎች ሥራ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በፓርኮቹ 6 ዩኒየኖች እና 67 የህብረት ሥራ ማህበራትን ጨምሮ በአጠቃይ 272 ሺህ 635 አርሶ አደሮች በግብዓት ትስስር መፍጠራቸውን አመልክተዋል፡፡

በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተጨማሪ 31 ፋብሪካዎች በቅርቡ ሥራ ለመጀመር አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢንዱስትሪዎች በተኪ ምርት ላይ በስፋት እንዲሳተፉ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሯ÷ በዚህም አመርቂ ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በተለያዩ ዘርፎች በተኪ ምርት ላይ በተከናወኑ ሥራዎች 1 ነጥብ 08 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማዳን መቻሉን አብራርተዋል፡፡

ከኢንዱስትሪ ፓርኮች በወጪ ንግድ 47 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን ÷ በሥራ እድል ፈጠራም የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.