Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ጥቃትና ዲጂታል ማጭበርበርን ለመከላከል እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችና ዲጂታል ማጭበርበርን ለመከላከል በትኩረት እየሰራሁ ነው አለ።

ባንኩ የሳይበር ደህንነት ወርን ለ2ኛ ጊዜ ”ተዓማኒ የባንክ አገልግሎት በዜሮ ትረስት ደህንነት” በሚል መሪ ሀሳብ እያከበረ ነው።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተወካይና የኮርፖሬት አገልግሎቶች ኤክስኪውቲቭ ም/ ፕሬዚዳንት አቶ አፍሬም መኩሪያና የሌሎች ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

አቶ አፍሬም በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስተማማኝና ዘመኑን የዋጀ ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ ነው።

በተለይም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው ብለዋል።

አሁን ላይ የባንኩ 90 በመቶ ግብይት በዲጂታል አማራጭ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ከዚህ ጋር ተያይዞም የሳይበር ጥቃትና የዲጂታል ማጭበርበር ስጋት ተጋላጭነት እየጨመረ መምጣቱን አመልክተዋል።

ችግሩን ለመከላከል ንግድ ባንክ ዘመኑን የሚመጥን የቴክኖሎጂ ሥርዓት በመዘርጋት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችንና ዲጂታል ማጭበርበርን ለመከላከል ትኩረት ተደርጓል ነው ያሉት።

የባንኩ ሳይበር ደህንነት ክፍል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚሰራ የዜሮ ትረስት ደህንነት ስትራቴጂ አዘጋጅቶ እየሰራ ነው ብለዋል።

ከጊዜው ጋር መልካቸውን እየቀየሩ የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችንና ዲጂታል ማጭበርበርን ለመከላከልም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ባለድርሻ አካላትም በዘርፉ አስፈላጊውን ግንዛቤ ለመፍጠር በትብብር እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.