ለካፒታል ገበያ ስኬት የሒሳብ ባለሙያዎች ሚና …
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የካፒታል ገበያ የታለመትን ግብ እንዲመታ ብቁ የሆኑ የሒሳብ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል አሉ የዘርፉ ምሁራን።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሒሳብ አያያዝ መምህር የሆኑት አየለ ከበደ እንዳሉት÷ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ለሚገኘው የካፒታል ገበያ እንቅስቃሴ የሒሳብ ሪፖርቶች ወሳኝ ናቸው።
ሪፖርቶቹን የሚያዘጋጁ ባለሙያዎችን መቆጣጠርና ብቁ እንዲሆኑ በማድረግ ካፒታል ገበያው ላይ በሚወጡ የሒሳብ ሪፖርቶች የካፒታሎችን ትክክለኛ እሴት ለማወቅ ብሎም ኢንቨስት ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።
የካፒታል ገበያ በተለይም በግብርና የተሰማራውን ማሕበረሰብ እንዲደግፍና ትርፋማነቱን እንዲያረጋገጥ በትክክለኛ መረጃ መሰረት ካፒታል እንዲገዙና እንዲሸጡ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የሒሳብ ሪፖርት የሚያዘጋጁ ባለሙያዎች ጥራት ያለው ትክክለኛ መረጃ ማቅረብ የሚችሉበትን እንዲሁም ተጠያቂ የሚደረጉበትን ሥርዓት ለመዘርጋት መሰል ተቋማትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የሕግ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን ነጋሽ በበኩላቸው÷ ካፒታል ገበያውን በዘላቂነት ለማስቀጠል ብቁ እና ሥነ ምግባራቸውን የጠበቁ የሒሳብ ባለሙያዎች ሊኖሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የአንድን ድርጅት የሒሳብ ወይም የኦዲት ሪፖርት የሚያዘጋጁ ባለሙያዎች ብቁ መሆን ካልቻሉ ዜጎች ኢንቨስት ለማድረግ ሲወስኑ በተሳሳተ ሃሳብ ላይ ገንዘባቸውን እንዲያወጡ ሊያደርግ ይችላል ነው ያሉት፡፡
በካፒታል ገበያ ውስጥ ካፒታል ለመግዛት በዋናነት የሒሳብ ሪፖርቶችን መመልከት ወሳኙ ርምጃ እንደሆነና የሒሳብ ሪፖርቶችም ለገዢዎች አስፈላጊውን ትክክለኛ መረጃ የሚያቀርቡ መሆን እንዳለባቸው የተናገሩት ደግሞ የሒሳብ አያያዝ ቦርድ ተጠባባቂ ዳይሬክተር ፈቃዱ አጎናፍር ናቸው።
አሁን ላይ እንደ ሀገር ታአማኒ የሆነ የሒሳብ ሪፖርት ማዘጋጀት የሚችሉ ብቁ የሒሳብ ባለሙያዎች እጥረት መኖሩን አመልክተዋል፡፡
በርካታ ዘርፎች ለውጪ ገበያ ክፍት በሚደረጉበት በዚህ ወቅት ዘርፉን በተሻለ መልኩ ለመከታተልና ለማሳደግ እንዲቻል ትክክለኛ የሒሳብ ሪፖርት የሚያቀርቡ የሒሳብ ባለሙያዎች እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!