Fana: At a Speed of Life!

ፋና 80 የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር በመጪው እሁድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለበርካታ ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው ፋና 80 የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር በመጪው እሁድ ይደረጋል፡፡

የፊታችን እሁድ የካቲት 29 በሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር ላይ አራት የውዝዋዜ ቡድኖች ውድድሩን በበላይነት ለማጠናቀቅ ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

አራቱ ቡድኖች እንደየደረጃቸው 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብሩን የሚከፋፈሉ ሲሆን፥ 1ኛ የሚወጣው ቡድን ለውድድሩ የተዘጋጀውን ዋንጫ የግሉ ያደርጋል፡፡

አሀዱ ዘመናዊ የዳንስ ቡድን፣ ኢትዮጵያን የባህል ቡድን፣ ነገስታት ዘመናዊ የዳንስ ቡድን፣ ሳባ ኖባ የባህል ቡድን የፍጻሜው ተፋላሚዎች ናቸው።

በዓለም አቀፍ የዳንስ ልምዱ የሚታወቀው ጁናይድ ጀማል በውድድሩ ላይ በተጋባዥ ዳኝነት የሚሳተፍ ሲሆን፥ የፍጻሜው ውድድር በዕለቱ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለተመልካቾች ይደርሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.