Fana: At a Speed of Life!

በሴዑል ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የሴዑል ማራቶን በወንዶች አትሌት ሀፍቱ ተክሉ በሴቶች አትሌት ሔቨን ኃይሉ አሸንፈዋል።

በወንዶች ውድድር አትሌት ሀፍቱ ተክሉ በ4 ዓመት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን÷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2:04:23 ወስዶበታል።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጌታነህ ሞላ 2:04:25 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ÷ አትሌት ፀጋዬ ታደሰ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል።

በሴቶቹ ውድድር ደግሞ አትሌት ሔቨን ኃይሉ 2:19:10 በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባ አሸንፋለች።

አትሌት በቀለች ጉደታ 2:19:40 በመግባት በውድድሩ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ÷ አትሌት ቦሰና ሙላቴ 2:19:48 በመግባት ሦስተኛ እንደወጣች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.