ሲመርጡ…
ምርጫ የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ሥርዓት መገለጫ ነው፡፡ ዜጎች ነጻ ሀሳባቸውን የሚገልጹበት እና ሀገር የሚያስተዳድሩ ብቁ ዕጩዎችን ለሥልጣን የሚያበቁበት አንዱ መንገድም ነው፡፡
ስለዚህ እርስዎም የምርጫ ካርድ ወስደው ሲመርጡ፡-
⚙️የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ቁልፍ ጽንሰ ሃሳብ እና እኩልነት እንዲረጋገጥ የድርሻዎን ይወጣሉ፤
⚙️በሀገርዎ የአስተዳደር ሥርዓት ላይ አሻራዎን ያኖራሉ፤
⚙️ሀገር በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንድትተዳደር እና ትውልድ ዘመናዊነትን እንዲለማመድ ያደርጋሉ፤
⚙️ተጠያቂነትና ኃላፊነት ያለበት በህዝብ የተወከለ መንግሥት እንዲቋቋም ድርሻ ይኖርዎታል፤
⚙️በተለያዩ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች የሚወክልዎን አስተዳደራዊ አካል ይመርጣሉ፤
⚙️መንግሥት ለዜጎቹ የሚጠቅሙ ፓሊሲዎች እንዲያዘጋጅና እንዲተገበሩ ያደርጋሉ፡፡
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተመዝግበው የምርጫ ካርድዎን ካልወሰዱ ጊዜው አሁን ነው!
በምርጫ ብቻ!