2 ሺህ ጉንዳኖችን ለመዝረፍ የሞከረው ቻይናዊ ክስ ተመሰረተበት
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ2 ሺህ በላይ ጉንዳኖችን ከኬንያ በሕገ ወጥ መንገድ ለማስወጣት የሞከረው ቻይናዊ ክስ ተመስርቶበታል፡፡
ዣንግ ኬኩን የተባለው ቻይናዊ 2 ሺህ ጉንዳኖችን በከረጢት በማሸግ ከኬንያ ለማስወጣት ሲሞክር በናይሮቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ሥር ውሎ ፍ/ቤት መቅቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ግለሰቡ ጉንዳኖቹን ቻርለስ ምዋንጊ ከተሰኘ ኬንያዊ በ10 ሺህ የኬንያ ሽልንግ መግዛቱ ነው የተመላከተው፡፡
የኬንያ ባለስልጣናት ከአውሮፓ እና እስያ ሀገራት መሰል ፍላጎቶች መበራከታቸውን በመጠቆም ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡
ድርጊቱን ተከትሎም ዣንግ ኬኩንና ኬንያዊ ግብረ አበሩ ቻርለስ ምዋንጊ 2 ሺህ ጉንዳኖችን ከኬንያ በሕገ ወጥ መንገድ ለማስወጣት መሞከር የሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
የተከሳሹ ጠበቃ ዴቪድ ሉስዌቲ በበኩላቸው÷ ዣንግ ኬኩን ድጊቱን የፈጸመው የሀገሪቱን ሕግ ባለማወቁ ነው ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡
ዣንግ እና ምዋንጊ ከሳምንት በኋላ ዳግም ጉዳያቸው ሊታይ በፍርድ ቤት ቀጠሮ መሰጠቱንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
በአቤል ነዋይ