Fana: At a Speed of Life!

በቶተንሃም ሆትስፐር እየተፈለገ የሚገኘው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ…

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 21፤2018 (ኤፍ ቢሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር ጣሊያናዊውን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል፡፡

አሰልጣኝ ኢጎር ቱዶርን በትናንትናው ዕለት ያሰናበተው ቶተንሃም ሆትስፐር ሮቤርቶ ዲዘርቢን በቋሚነት የቡድኑ አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠር እንደሚፈልግ ተነግሯል፡፡

ኢጎር ቱዶር በሰሜን ለንደኑ ክለብ የ44 ቀናት ቆይታቸው ደካማ ውጤት በማስመዝገባቸው ከቡድኑ መሰናበታቸው ይታወቃል፡፡

ዲዘርቢ ቶተንሃም ሆትስፐርን ለመረከብ ፍላጎት ቢኖራቸውም ነገር ግን ክለቡ በሊጉ መቆየቱን ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ ቢቢስ ስፖርት ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ የፕሪሚየር ሊጉን ክለብ ብራይተንን ጨምሮ ኦሎምፒክ ደ ማርሴ፣ ፓሌርሞ፣ ሳሶሎ እና ሻካታር ዶኔስክ የመሳሰሉ ክለቦችን አሰልጥነዋል፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር በዚህ የውድድር ዓመት በሊጉ 30 ነጥብ በመሰብሰብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.