Fana: At a Speed of Life!

በምርጫው ሕዝብ የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት እንደሆነ ታይቷል – ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የታየው የሕዝብ የነቃ ተሳትፎ የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት ሕዝብ እንደሆነ ያሳየ ነው አሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች።

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ሰላማዊና ንቁ የሕዝብ ተሳትፎ የታየበት መሆኑን ተናግረዋል።

የኩሽ ሕዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ ም/ፕሬዚዳንት አስፋው ፍጋ እንዳሉት÷ ሕዝቡ ከማለዳ ጀምሮ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን ይሆነኛል ላለው ፓርቲ በመስጠት የስልጣን ባለቤት መሆኑን በተግባር አረጋግጧል ብለዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ በትውልድ አካባቢያቸው ተገኝተው ድምጻቸውን እንደሰጡና ምርጫው ፍጹም የተረጋጋና ሰላማዊ መሆኑን አንስተዋል።

ምርጫ የተሻለ ሃሳብ አሸናፊ ሆኖ የሚወጣበት ሥርዓት ነው ያሉት ደግሞ የሕብር ኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ፓርቲ የጌዴኦ ዞን ተወካይና የዞኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ መስከረም ተዘራ ናቸው።

በጉጉት የጠበቅነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ነጻና ገለልተኛ እንዲሁም በተረጋጋ መንገድ መካሄዱ የዴሞክራሲ ባህል እየጎለበተ መምጣቱን ያሳያልም ነው ያሉት፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ(ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ በምርጫው የታየው የሕዝቡ የነቃ ተሳትፎ ሕዝብ የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብለዋ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.