ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ድምጽ ሰጠች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በሚገኘው የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅ ሰጥታለች።
አትሌቷ ምርጫ በየአምስት ዓመቱ አንዴ የሚመጣ በመሆኑ ሕዝቡ ይሰራልኛል፣ ይወክለኛል የሚለውን አካል በተመቸው መንገድ የሚመርጥበት ልዩ ዕለት ነው ብላለች።
በምርጫ ድምፅ ስትሰጥ ይህ ለ7ኛ ጊዜ መሆኑን ጠቅሳ በዘንድሮው ምርጫ ለምርጫ ዕድሜ የደረሱ ልጆቿን በማስከተል በጋራ ድምፅ መስጠቷ እጅግ ያስደሰታትና የተለየ እንደሆነ ተናግራለች።
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision