Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው በነጻነት መከናወኑ ዴሞክራሲያዊ ልምምድን ያጠናከረ ነው – የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በነጻነት መከናወኑ የሀገር ግንባታና የዜጎች ዴሞክራሲያዊ ልምምድን ያጠናከረ ነው አለ የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት።

ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እና የሶዴፓ ፓርቲ ተወካይ አቶ በለጠ ሲጌቦ የምርጫውን ሂደት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ÷ ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ ንቁ የሕዝብ ተሳትፎ የተደረገበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በክልሉ ካሉት 23 የፖለቲካ ፓርቲዎች 18 የሚሆኑት እጩ በማቅረብ በምርጫው መወዳደሩን ገልጸው÷ ምርጫው ሀገር ያሸነፈችበት ነው ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በክልሉ 19 የምርጫ ክልሎች በሚገኙ 2 ሺህ 266 ምርጫ ጣቢያዎች እንዲታዘቡ በተመቻቸው ሁኔታ በመታዘባቸው ምርጫው ያለምንም ችግር መፈጸሙን አመልክተዋል።

መራጩ ምንም ሳይበግረው ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ምቹ ሁኔታን በሚፈጥር ሂደት ላይ የነበራቸው ተሳትፎ ለቀጣይ ዴሞክራሲን ለማጽናት ያመቻቸ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በጌታቸው ሙለታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.