Fana: At a Speed of Life!

የመራጮች ተሳትፎና ተነሳሽነት ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትልቅ ተስፋ ነው – ፌዴሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የነበረው የመራጮች ተሳትፎና ተነሳሽነት ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትልቅ ተስፋ ነው አለ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን፡፡
የፌዴሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ገነት ስዩም እንዳሉት፤ ፌዴሬሽኑ በመራጮች ትምህርት እና በታዛቢነት በመሳተፍ ሴቶች በምርጫው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል።
ፌዴሬሽኑ በነበረው የታዛቢነት ሚና በአብዛኛዎቹ የምርጫ ክልሎች ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁንና የህዝብ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ተናግረዋል።
የመራጮች ተሳትፎና ተነሳሽነት የሚደነቅ መሆኑን ገልፀው፤ ይህም ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ትልቅ ተስፋ ነው ብለዋል።
በመራጭነትም ሆነ በታዛቢነት የሴቶች ተሳትፎ አበረታች ነበር ብለዋል።
ፌዴሬሽኑ በ25 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን ታዝቧል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በአብዛኞቹ ጣቢያዎች ቆጠራው በግልጽነት መካሄዱን፤ የፓርቲ ወኪሎች እና ታዛቢዎች በቆጠራ ሂደቱ ውስጥ መሳተፋቸውን መታዘብ መቻሉን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሚነሱ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ መስጠቱ በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል ነው ያሉት።
በሔብሮን ዋልታው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.