Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶች በሚያደርጉት የነቃ ተሳትፎ ሀገር ይገነባል – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በወቅታዊ የልማትና የሰላም ሥራዎች ዙሪያ ከወጣቶች ጋር በባሕር ዳር ተወያይተዋል፡፡
በመድረኩ የሰላም እና የልማት ሥራዎችን በትጋት በማከናወን ሀገርን ወደ ላቀ ከፍታ ለመውሰድ የወጣቶች ሚና ምን መሆን እንዳለበት ተነስቷል።
በዚሁ ወቅት አቶ አረጋ ከበደ ፥ በወጣቶች ሁለንተናዊና የነቃ ተሳትፎ ሀገር ይገነባል፤ የሕዝብ ሰላም በዘላቂነት ይረጋገጣል፤ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችም ከዳር ይደርሳሉ ብለዋል።
የባሕር ዳር ከተማ ብሎም የክልሉ ወጣቶች በትላልቅ ሀገራዊ ሁነቶች በንቃት የሚሳተፉ፣ በውጤትም አጅበው ሥራዎችን የሚፈጽሙ ናቸው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወጣቶች በተለይም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላሙ የተጠበቀ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ሚናቸው ከፍተኛ እንደነበር አንስተው÷ ከመሪዎቻቸው ጋር በመተባበር የልማት ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ አንስተዋል።
ወጣቶች በሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑና የራሳቸውን ብሎም የሀገራቸውን ኢኮኖሚያዊ ልዕልና እንዲያረጋግጡ እንሠራለን ነው ያሉት፡፡
ለሕዝብ ሰላምና ልማት የሚተጉ ወጣቶች የሀገር መሠረቶች ናቸው፤ ወጣቶች ሀገርን በሚጠቅሙ ዘርፎች ላይ ሁሉ በንቃት በመሳተፍ የልማት አርበኛ ሊሆኑ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.