Fana: At a Speed of Life!

ከለነገዋ የተመረቁ ሴቶች አዲስ አበባን ለዘመናት የከረሙ ስብራቶቿ የሚጠገኑባት ከተማ የማድረግ ማሳያ ናቸው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)አዲስ አበባ ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት እንዲሁም ለዘመናት የከረሙ ስብራቶቿ የሚጠገኑባት ከተማ የማድረግ የተግባር ውጤት ፍሬ ማሳያዎች ከለነገዋ ተመርቀው አዲስ ህይወት እየመሩ ያሉት ሴቶች እህቶቻችን ናቸው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤በተለያዩ ማህበራዊ ችግር ውስጥ የነበሩ በለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ5ኛ ዙር የክህሎት እና የስብዕና ግንባታ የሰለጠኑ 858 እህቶቻችንን አስመርቀን ወደ ስራ አሰማርተናል ብለዋል።
በከተማችን ከምንሰራቸው ሰው ተኮር ስራዎች አንዱ ትላንት በጎዳና፣ በችግር እና በተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ የነበሩ ሴቶችን በሙያ ክህሎትና ስብዕና ገንብተን ከነበሩበት አስከፊ ህይወት በማውጣት ወደ ተሻለ ህይወት የምናሰማራበት ቀዳሚው ተግባር ነው ብለዋል።
የዛሬዎቹ ተመራቂዎችን ጨምሮ በማዕከሉ በድምሩ 3 ሺህ 259 ሰልጣኞችን አስመርቀን ወደ ስራው ዓለም እንዲቀላቀሉ በማድረግ ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲመሩና ለሌሎችም አርዓያ እንዲሆኑ አድርገናል ነው ያሉት፡፡
አስከፊውን ትላንታችሁን አልፋችሁ፤ በማዕከሉ በነበራችሁ ቆይታ በቀሰማችሁት ክህሎት እና ባገኛችሁት የተሀድሶ ስልጠና ዛሬ ማሸነፍ ችላችኋል፤ ነገም በስራው ዓለም ስኬታማ ለመሆን የሚገጥማችሁን ማንኛውንም ፈተና አሸንፉችሁ ህይወታችሁን ይበልጥ ብሩህ እንደምታደርጉ እናምናለን ሲሉም ተናግረዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.