ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሕንድ ገቡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ኒው ዴልሂ ሕንድ ገብተዋል።
ጉባዔው “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚካሄደው፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከጉባዔው ጎን ለጎን ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን የሚያጠናክሩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።